National Opportunities

Tender Notice Board

Discover the latest public procurement and private sector tenders from across Ethiopia. Register to unlock full details.

Search Tenders

Browse Categories

Showing 1 to 12 of 90 opportunities
Disposal SalePlastics & Plastic ProductssaleSteel/ Metals & AluminumWood & Wood Related Recently

ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር   ያገለገሉ እንጨት  ፓሊት እና ሎችም  እስክራፐ እነቶች (IBC& wooden pallet sales plastic IBC=103 use, .Almunium Covered  IBC used .Wooden Pallet=150 used and .scrap pallet wooden=bundl ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Repi Soap and Detergent PLC

የጨረታ ማስታወቂያ ቀን፦ 17/09/2018 ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር   ያገለገሉ እንጨት  ፓሊት እና ሎችም  እስክራፐ እነቶች (IBC& wooden pallet sales plastic IBC=103 use, .Almunium Covered  IBC used .Wooden Pallet=150 used and .scrap pallet wooden=bundl ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ተጫረቾች፡- የ2018 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ያለው መሆኑ ይኖርበታል፡ የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO መልክ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፤ ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖረተር ጋዚጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ብቻ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ክፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ጨረታው እስከ ግንቦት  26,2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ግንቦት 26,2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00 ሰአት ዝግ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 9፡00አቅርቦትና ክምችት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ ሲሞሉ ከ ቫት በፊት መሆን አለበት፡፡ ለበለጠ መረጃ   ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ አድራሻ አዲስ አበባ ጅማ መንገድ ካራ ቆሬ ሰኘላይ ቼን  ክፍል ስልክ ቁጥር 0113693518 እና 0992921872

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosureHouse & Building ForeclosureIndustry & Factory Foreclosuresale Recently

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia

  የሐራጅ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡     ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት  አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት አድራሻ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የይዞታው ስፋት (ካ.ሜ) የይዞታው አይነት/ የሚሰጠው አገልግሎት 1. አቶ ተመስገን ጫላ ጃለታ ተበዳሪው ሸገር ከተማ ፉሪ/ክ/ከ የቀድሞ ወረዳ 4 L/349/2003/B6/P1 468 መኖሪያ ቤት 21,582,351.71 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 2. አቶ በለጠ ማሞ ፈይሳ በአለቃ ማሞ ፈይሳ በአዲስ አበባ ከተማ፣የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የካ/239500/12 346.21 መኖሪያ ቤት 9,488,058.72   28/9/2018 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት 3. አሌክሳንድራ ታደሰ ባዶ ተበዳሪዉ ሃዋሳ ከተማ፣ ታቡር ክ/ከተማ ሂማታ ቀበሌ 8580 150 መኖሪያ ቤት 2,724,365.26 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 4. አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ ተበዳሪዎች ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ WBIFBG/A/L/937/09 5000 ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ 38,071,965.73 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 5. ሃይለማሪያም ክንዴ ተበዳሪው በደብረ ማርቆስ ከተማ ተድላ ጓሉ ክ/ከተማ ቀበሌ 12 K/2004 200.00 የመኖሪያ ቤት  2,389,326.28 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 6. አቶ ሀብታሙ እንየው ምህረቴ ወይ አገሬ ደምለው በባህርዳር ከተማ፣ ጣና ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 16 AM001060516004 255.98 መኖሪያ ቤት 6,814,310.66   28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት   በመሆኑም፡- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡ ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነው፤ በተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ፣በተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ፣ በተራ ቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ሲሆን በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰዉ ንበረት ጨረታዉ የሚከናወነዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነው፡፡ የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡ ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ንብረቶቹን በጨረታ

Closing Date

Check Details

Bank RelatedComputerDisposal SaleGeneratorsOffice furniturePrinting & Publishing Recently

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ ካዝናዎች፣ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች (የመሽ ወንፊት፣ የፋቢሪክ እና የቆዳ)፣ ጠረጴዛዎች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ካዉንተር እና ኬጂ ከነ ጥበቃ ቤቶች እና ከሌሎች ቁርጥራጭ ብረቶች ጋር፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታ

Cooperative Bank of Oromia

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር FA- 10/2025/26 የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ ካዝናዎች፣ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች (የመሽ ወንፊት፣ የፋቢሪክ እና የቆዳ)፣ ጠረጴዛዎች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ካዉንተር እና ኬጂ ከነ ጥበቃ ቤቶች እና ከሌሎች ቁርጥራጭ ብረቶች ጋር፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነ በርሜሎቹ ጋር፣ አሮጌ ጋዜጣዎች፣ ባዶ የቶነር እቃዎች፣ የሽንት ቤት መቀመጫዎች እና የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፣ የወለል የፕላስቲክ ታይልስ፣ ኮሪደሮች እና በረንዳ ላይ የሚቀመጡ የአበባ ማሳደጊያ ሳህኖች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።  ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል: – የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን  በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ። የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ሱሉልታ አካባቢ ሁለት ቦታ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች  ሹፉኔ ቻይና ጋራጅ 100 ሜትር ገባ ብሎ አነን ሰላሌ የወተት ማቀነባበሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገዱ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት  ግንቦት 3፣ 5 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ግንቦት  10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ። እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቄራ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ። ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ። ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ)ዉን  በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosureHouse & Building ForeclosureIndustry & Factory Foreclosuresale Recently

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia

                                            የሐራጅ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት አድራሻ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር/መለያ  የይዞታው ስፋት የይዞታው አይነት/የሚሰጠው አገልግሎት 1. አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ ተበዳሪዎች ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ WBIFBG/A/L/937/09 5000 ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ 38,071,965.73 03/11/18 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 2. አቶ ማስረሻ ታደሰ ተበዳሪው ፍቼ ከተማ ቡርቃ ጉራ ወረዳ 1356/M-27/2006 400 የንግድ ህንጻ 1,960,015.85 03/11/18 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት 3. አቶ ተመስገን ጫላ ጃለታ ተበዳሪው ሸገር ከተማ ፉሪ/ክ/ከ የቀድሞ ወረዳ 4 L/349/2003/B6/P1 468 መኖሪያ ቤት 21,582,351.71 03/11/18 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት 4. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ተበዳሪው አርሲ ዞን ሳጉሬ ከተማ ቀበሌ 02 5/3066/001/2441/2015 209 የንግድ ቤት 1,814,003.20 03/11/18 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት 5. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ነፃነት ናስር አርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 10651/91/97 200 መኖሪያ ቤት 2,567,870.84 03/11/18 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት በመሆኑም፡- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡ ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩ ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ሲሆን በተራ ቁጥር 4-5 የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው አሰላ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ነው፡፡ የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡ ከመኖሪያ ቤት ውጪ ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ሰዉ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋ/መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡ በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡   እርማት፡ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በታተመው የሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ በተ.ቀ. 5 ላይ የተገለጸው አቶ ጌቱ ሃይሌ ጨራኮ ለወሰዱት

Closing Date

Check Details

Bank RelatedForeclosuresaleVehicle ForeclosureVehicle Sale Recently

ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበውን ተሽከርካሪ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Bunna Bank

የሐራጅ ማስታወቂያ  ቁጥር፤ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/040/2018                    ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበውን ተሽከርካሪ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተሽከርካሪ   ተ.ቁ   የተበዳሪ ስም   የንብረት አስያዥ ስም   አበዳሪ ቅርንጫፍ   የሰሌዳ ቁጥር   የመያዣ አይነት/ሞዴል   የሻንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥር   የሞተር ቁጥር   የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር   የጨረታ ቀን እና ሰዓት   ጨረታው የወጣው       1   አቶ ብርሃኑ ሶረቶ ሶመኖ     ተበዳሪ   ወሎ ሰፈር   ኢት-03-A18437   የ2022 ምርት ሲኖ ትራክ   LZZ5BLSF2NW074978   WD61 5.47*2208070437 87*     7,000,000.00   ሰኔ 17   ቀን 2018 ዓ.ም   4፡00-5፡00     ለመጀመሪያ ጊዜ   የሐራጅ ደንቦች፣ ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት፡፡ ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ፡፡ ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡ በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡ የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡ በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡ ጨረታው በቡና ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፤ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ሩዋንዳ መታጠፊያ ሳይደርሱ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ፣ ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

Closing Date

Check Details

Disposal SaleGeneratorssale Recently

ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’  ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Berhan International Bank S.C

ያገለገሉ ጀነሬተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ-10/18 ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’  ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡   ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች፤ ዝርዝራቸዉ፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ጀነሬተሮች የሚገኙት ገላን ከተማ ቱሉ ጉራቻ ቀበሌ ኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን ሲሆን፣ ከታች በ9ነኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱት ስልክ ቀጠሮች በቅድሚያ ደዉለዉ ቀጠሮ በማስያዝ ማየት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ግቢ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ጀነሬተር የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ፤ ጀኔሬተሮች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ P.O ጋር፣ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡ ጨረታዉ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ባስገቡበት፣ በ5ተኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሰዉ አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል፡፡   ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን ጀነሬተር/ጀነሬተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፣ 0918890721 / 0998411523 / 0114437439 / 0116631729 ይደዉሉ፡፡

Closing Date

Check Details

Bank RelatedForeclosuresaleVehicle ForeclosureVehicle Sale Recently

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia

የሐራጅ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡     ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት  አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት የሰሌዳ ቁጥር ሞተር ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የንብረቱ አይነት የሥሪት ዘመን 1. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ወንድም ፈለቀ አአ-02- C33705 G4LANM147995 MALB241C8NM149028 ሃዩንዳይ ግራንድ i10 አዉቶሞቢል 2022 3,098,304.00 17/10/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 2. አቶ ናስር ካሊል ሞሐመድ ተበዳሪው 02-AA-B76699 JFC92432. 1FTEX1EP1JFC92432 ፎርድ F150 ኪንግ ካፕ 2018 4,765,200.00 17/10/2018 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት 3. ኳድራንት አፓርል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪው ኢት-03-66900       እና ኢት-03-20264 F3BEE681G*B220222647* WjME3TRE8EC286633 እና  TT-1044-14 የጭነት እና ተሳቢ ተሽከርካሪ 2014 11,033,376.00 17/10/2018 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት በመሆኑም፡- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡ ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነዉ፡፡ የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡  

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosureHouse & Building Foreclosuresale Recently

ስኬት ባንካ አ.ማ (የቀድሞ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ) ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና እንደተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Siket Bank

የሐራጅ መስታወቂያ ስኬት ባንካ አ.ማ (የቀድሞ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ) ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና እንደተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ/ቁ የተበዳሪው ስም የዋሱ ስም የቤቱ ዓይነት ብድሩ የወጣበት ቅርጫፍ        ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት መነሻ ዋጋ ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ ምርመራ ከተማ፣ክ/ከተማ ክ/ከተማ    የቤቱ ካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ     ቀን ሰዓት   1     ኢትቻ መርጋ   አማሩ እሼቱ   መኖሪያ ቤት   አለምገና   አዋሽ መልካ     አዋሽ መልካ   BMA/0031/09   200   362,208   06/11/2018   4፡00   በድጋሚ   2 ነቢል ሙንትሀ እና ጓደኞቻቸዉ ህ/ሽ/ማህበር መዲና መሀመድ   መኖሪያ ቤት   አየርጤና   ሸገር   ፉሪ   L/S/27024/2002   140   4,345,075   06/11/2018   4፡30   በድጋሚ 3 ገነት አስቴር እና ጓደኞቻቸዉ ህ/ሽ/ማ ወርቁ ሀዋስ መኖሪያ ቤት ቢሾፍቱ   ቢሾፍቱ   ጨለለቃ   161   420   407,045   06/11/2018   5፡00 በድጋሚ 4 ገቢሳ ካዎ አዋሱ ካዎ መኖሪያ ቤት አለምገና ሸገር ፉሪ ሰ/ኮ/0867/05 50.98  2,012,690 07/11/2018 4፡30 በድጋሚ   5   መሀመድ ሸዋ   በራሳቸዉ   መኖሪያ ቤት   ቤ/ሚካኤል   ሸገር   ፉሪ   ሰ/ኮ/0164/05   49.51   1,585,557   07/11/2018   6፡00   በድጋሚ 6 ረታ ከፈኒ በራሳቸዉ መኖሪያ ቤት ሰንዳፋ ሰንዳፋ በኬ   01   155/142/2012   140   207,323   08/11/2018   5፡00   በድጋሚ   7   ፍቃዱ ቶሌራ   ሰብለ አማረ   መኖሪያ ቤት   ቢሾፍቱ   ሞጆ   ቀርሳ   OR021024005014   199.12   4,433,669   09/11/2018   6፡00   ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳሰቢያ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የቤቱን ሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መጫረት ይችላል ፡፡ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታዉን ማሸነፉቸዉን በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈሉ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡ ተራ ቁጥር 1፣2፣3 ላይ የሚገኙት ቤቶች ጨረታዉ የሚካሄደዉ ፒያሳ ቸርችል ጎዳና በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ሲሆን፣ተራ ቁጥር 4፣5፣6፣7 ላይ የሚገኙትን ጨረታዉ መኖሪያ ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ይከናወናል፤የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታዉ መክፈቻ ስላሳ ደቂቃ ቀደም ብሎ ይጀመራል፡፡ ንብረቱ በገዢዉ ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተዉ መንግስት አካል ደብዳቤ ይፅፋል ፡፡ ቤቱን ለማየት ሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታዉ ከሚከናወንበት 5(አምስት) ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት ህግ ክፍል በመመዝገብ ባንኩ በሚያመቻቸዉ ፕሮግራም ቤቶችን መጎብኝት ይቻላል፤በተጨማሪም ብድሩ በተሰጠበት ቅርጫፍ ፅ/ቤት በስራ ቀናት በመሄድ ቅርንጫፉ በሚሰጠዉ ፕሮግራም መሰረት መጎብኝት ይቻላል፡፡ ስም ማዘዋወሪያ፤የሊዝ ክፍያ እና ሌሌች ዉዝፍ ክፍያዎች እንዲሁም ገዥ እንዲከፈላቸዉ በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ገዥዉ/አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ በጨረታዉ የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ጨረታውን ካካሄደዉ የባንኩ የሕግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይሆናል፡፡ በጨረታዉ ቀን የንብረቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ በመገኝት ጨረታዉን መከታተል ይችላሉ ባይገኙም ጨረታዉ ይካሄዳል፡፡ ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 8342 ወይም 011-1-279028 በመደወል ወይም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕግ አገልግሎት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ  ይቻላል፡፡                     

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosureHouse & Building Foreclosuresale Recently

ጸደይ ባንክ አ.ማ ለወ/ሮ መሰረት ተሻገር ለሰጠው ብድር በዋስትና ያስያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በካርታ ቁጥር k/አብ-01007 የተመዘገበ በአዋሳኝ በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያሳብ አያሌው፣ በሰሜን ዳዊት አያሌው፣ በደቡብ ሽበሽ ገላየ የሚያዋስነው ስፋቱ 150 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድጋሚ ለ2

Tsedey Bank S.C

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ፡፡ ጸደይ ባንክ አ.ማ ለወ/ሮ መሰረት ተሻገር ለሰጠው ብድር በዋስትና ያስያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በካርታ ቁጥር k/አብ-01007 የተመዘገበ በአዋሳኝ በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያሳብ አያሌው፣ በሰሜን ዳዊት አያሌው፣ በደቡብ ሽበሽ ገላየ የሚያዋስነው ስፋቱ 150 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች  መገንዘብ ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ፡፡ የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 3,452,861.48 /ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አምሳ ሁለት ሺ ስምንት መቶ ስልሳ አንድ ከአርባ ስምንት ሳንቲም/ ነው ፡፡ በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት ፡፡ የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል ፡፡ የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል ፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው 1/4ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል ፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል ፡፡ የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡ ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ ፡፡ ጨረታው የሚካሄደው ደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 13 ለጨረታ በወጣው ንብረት ውስጥ ነው ፡፡ ጨረታው የሚካሄደው ሃምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር  0912436868 / 0921667115 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

Closing Date

Check Details

Construction Machinery & EquipmentDisposal SaleMachineryOffice furnitureTransport Services Recently

The Development Bank of Ethiopia intends to sell the following properties that it has acquired from a defaulter pursuant to the power vested in it by proclamation No. 97/98, 216/2000 and 1147/2019.

Development Bank Of Ethiopia

Bid Announcement The Development Bank of Ethiopia intends to sell the following properties that it has acquired from a defaulter pursuant to the power vested in it by proclamation No. 97/98, 216/2000 and 1147/2019. S. N Name of former Borrower’s/ Guarantor’s Name Type (categorty)  of Properties Plate No. Bid Floor Price (Birr) Property location Bid Type Date and Time of Bid 1 M2K Engineering PLC Machineries and equipment   Birr 34,781,495.00 (Thrity Four Million Seven Hundred Eighty One Thousand Four Hundred Ninty Five Birr) Gelan town in the – M2K Engineering Factory Premises Negotiation   May  11, 2026 From 10:00 –    12:00 AM 2 Office Furniture   Birr 650,051.00 (Six Hundred Fifty Thousand Fifty One Birr) Gelan town in the – M2K Engineering Factory Premises   Negociation May 12,2026 from 10:00-12:00 AM                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                              3 Forklift   Birr 210,396 (Two Hundred Ten Thousand Three Hundred Ninty Six Birr) 4 Generator   Birr 697,151.00 (Six Hundred Ninty Seven Thousand One Hundred Fifty One Birr) 5 Mini bus 3-77195AA Birr 763,853.00 (Seven Hundred Sixty Three Thousand Eight Hundred Fifty Three Birr) Lega Tafo Legedadi town–(in the former MNS Textile Factory Premises 6 Mini bus 3-65018AA Birr 2,202,545.00 (Two Million Two Hundred Two Thousand  Five Hundred Fourty Five Birr)   7 Cargo truck 3-77197AA Birr 410,562.00 (Four Hundred Ten Thousand Five Hundred Sixty Two Birr) Gelan town – in the M2K Engineering Factory premises   8 Cargo truck 3-77150AA Birr 342,940.00 (Three Hundred Fourty Two Thousand Nine Hundred Fourty Birr) 9 Cargo truck 3-77196AA Birr 345,355.00 (Three Hundred Fourty Five Thousand Three Hundred Fifty Five Birr)   Instruction to bidders:- Interested bidders can obtain a complete bid document of the property, during office hours of the Bank upon payment of non-refundable fee of Birr 100.00 (Birr One Hundred) in cash, and fill out the bid document with their name, the offer price and other information as required by the format. The complete Wax-sealed bid document shall be received until May 11, 2026 9:50 A.M for machineries (Item-1) and May 12,2026  50 A.M for the others(Items #2-9), through bid placed at the Bank’s Head Office, second tower, ground floor starting from the third day of publication of this bid announcement. The bids shall open on May 11 and 12,2026 at 10:00 A.M Bidders shall submit 10% ( ten percent) of the floor price of the properties only in CPO as a bid security. A winner shall deposit the remaining winning price in full within 15 (Fifteen) calendar days from the date of award. Failure to deposit the amount within the specified time frame shall be a cause for loss of a bid security and cancellation of the award (bid). The bid shall take place at the Head Office of the Development Bank of Ethiopia, Tower Two, 5th Floor, on the date and time specified in the table above. Only the bidders or their authorized legal representatives shall be allowed to attend the bid process The winner is required to pay 15% VAT (Fifteen Percent Value Added Tax), and all other legal and administrative fees and charges in accordance with applicable laws. Some components of the properties have been procured under duty free scheme. Thus, the winner should either have matching custom duty exemption privilege or else shall be bound to pay the outstanding duties & taxes. The Bank intends to sell the properties on a cash basis only. The bank will write a letter to the concerned government body to facilitate transfer of the title of the properties to the buyer. It shall be the buyer’s responsibility to follow-through the process and get it finalised. The winner shall cover all costs of dismantling, loading unloading and transporting the properties to own distination. The properties are availed for sale separately as indicated under their respective serial numbers. bidders can obtain more information from the Development Bank of Ethiopia, Ongoing Concern Projects and Acquired Assets Management Directorate, 2nd Tower 3rd Floor or through telephone 011-524-53-73/011-524-42-69. Bidders can also visit the properties by making an appointment with the bank in advance.. The Bank reserves the right to cancel the bid partially or fully. THE DEVELOPMENT BANK OF ETHIOPIA

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosuresaleVehicle Foreclosure Recently

    ወጋገን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Wegagen bank

                                           ወጋገን ባንክ አ.ማ                         ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ                               ቁጥር፡ ወጋገን 025/2018        ወጋገን ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡            ተ.ቁ የተበዳሪው ስም ንብረት አስያዥ አበዳሪ ቅርንጫፍ የተሽከርካሪ            ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ/ሴሪያል/ ቁጥር የሞተር ቁጥር ዘመን የነዳጅ አይነት የጨረታ መነሻ        ዋጋ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን   ቀን ሰዓት 1 ኤን ኬይ ኤች ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪው ሰባራ ባቡር ድርብ ተግባር (ፒክአፕ) አአ-03-B33009 MR0DB9CD7M5151328 2GD-5010093 2021 ናፍጣ 3,800,000.00   ግንቦት 27         ቀን 2018     ዓ.ም   ከጧቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት     ማሳሰብያ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡ የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡ በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ ጨረታው የሚካሄደው፡ በወጋገን ባንክ ዋና መስርያ ቤት 13ኛ ፎቅ ባለው የመሰብሰብያ አዳራሽ ይሆናል፡፡ ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡ ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይቻላል፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡   ወጋገን ባንክ አ.ማ  

Closing Date

Check Details

A House & Building SaleBank RelatedForeclosureHouse & Building ForeclosureIndustry & Factory Foreclosuresale Recently

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ(በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Global Bank Ethiopia S.C

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ(በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት የጨረታው መነሻ ዋጋ /ብር/ ጨረታ የሚከናወንበት ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ/ወረዳ ቀን ሰዓት 1 ወ/ሮ ሜሮን ሙላት ፍሰሃ ተበዳሪዋ ለቡ አ.አ ቂርቆስ 06 285 ካሬ ሜትር AA000040601166 የንግድና መጋዘን 31,360,864.49 ሐምሌ 1, 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 –5፡30 የጨረታ ደንቦች፡- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ። የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በጨረታው የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም። ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ይካሄዳል። በጨረታው ላይ ተጫራቾች፣ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ የያዘና በማሀበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል። የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ የተገለጸለት ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል። በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል። ለበለጠ ማብራሪያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 5 31 81 17 (የህግ አገልግሎት መምሪያ) ወይም 011 4 62 53 39 (ለቡ ቅርንጫፍ) ደውሎ መጠየቅ ወይም አበዳሪውን ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ ማነጋገርና ንብረቱን የሚጎበኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል። ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Closing Date

Check Details