Tender Notice Board
Discover the latest public procurement and private sector tenders from across Ethiopia. Register to unlock full details.
Search Tenders
ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩት ድርጅቱን እርጀከት ሰሊጥ (Reject Sesame Seed ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ቀን፦ 15/8/2018 ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩት ድርጅቱን እርጀከት ሰሊጥ (Reject Sesame Seed ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡– የ2018 የታደሰ ንግድ ፈቃድና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ያለውና ማቅርብ ይሚችል መሆን ይኖርበታል፡ የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ)ብር ማስያዝ ይኖርበታል፤ ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አራት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ብቻ በድርጅቱ አየር ጤና /ግራር ቅጥር ግቢ ተገኝተው የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ክፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ጨረታው እስከ ሚያዚያ 22,2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ሚያዚያ 22,2018 ዓ.ም ከሰዓት 6፡00 ሰአት ዝግ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 9፡00 አቅርቦትና ክምችት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ ሲሞሉ ከ ተ.እ.ታ በፊት መሆን አለበት እና ከዚህ በላይ የተዘርዘሩትን ህጎች ያላሞላ ተጫራች ዉድቅ ይሆናል፡፡ እቃወችን ማየት የሚቻለዉ ቀን ማክሰኞ እና እሮብ ብቻ ነዉ እና ባሸነፉት ዋጋ ለ 3 ወር ዉል ፈርሞ እቃዉ በተገኝ ግዜ ማንስት የሚችል ፡፡ እቃዉን ማየት የሚቻለዉ ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር አለም ገና ግቢ ዉስጥ እና ታይም ኤክስ ግቢ(Timex warehouse) ነዉ. ማሳሰብያ– ዋጋ ከነቫቱ ያስገባ ተጯራች ዉድቅ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ አድራሻ አዲስ አበባ ጅማ መንገድ ካራ ቆሬ ስልክ ቁጥር 0912161590
Closing Date
Check Details
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት አድራሻ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የይዞታው ስፋት (ካ.ሜ) የይዞታው አይነት/ የሚሰጠው አገልግሎት 1. አቶ ተመስገን ጫላ ጃለታ ተበዳሪው ሸገር ከተማ ፉሪ/ክ/ከ የቀድሞ ወረዳ 4 L/349/2003/B6/P1 468 መኖሪያ ቤት 21,582,351.71 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 2. አቶ በለጠ ማሞ ፈይሳ በአለቃ ማሞ ፈይሳ በአዲስ አበባ ከተማ፣የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የካ/239500/12 346.21 መኖሪያ ቤት 9,488,058.72 28/9/2018 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት 3. አሌክሳንድራ ታደሰ ባዶ ተበዳሪዉ ሃዋሳ ከተማ፣ ታቡር ክ/ከተማ ሂማታ ቀበሌ 8580 150 መኖሪያ ቤት 2,724,365.26 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 4. አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ ተበዳሪዎች ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ WBIFBG/A/L/937/09 5000 ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ 38,071,965.73 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 5. ሃይለማሪያም ክንዴ ተበዳሪው በደብረ ማርቆስ ከተማ ተድላ ጓሉ ክ/ከተማ ቀበሌ 12 K/2004 200.00 የመኖሪያ ቤት 2,389,326.28 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት 6. አቶ ሀብታሙ እንየው ምህረቴ ወይ አገሬ ደምለው በባህርዳር ከተማ፣ ጣና ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 16 AM001060516004 255.98 መኖሪያ ቤት 6,814,310.66 28/9/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት በመሆኑም፡- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡ ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱት ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነው፤ በተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ፣በተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ፣ በተራ ቁጥር 5 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ሲሆን በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰዉ ንበረት ጨረታዉ የሚከናወነዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነው፡፡ የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡ ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ ንብረቶቹን በጨረታ
Closing Date
Check Details
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ ካዝናዎች፣ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች (የመሽ ወንፊት፣ የፋቢሪክ እና የቆዳ)፣ ጠረጴዛዎች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ካዉንተር እና ኬጂ ከነ ጥበቃ ቤቶች እና ከሌሎች ቁርጥራጭ ብረቶች ጋር፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር FA- 10/2025/26 የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ጀነሬተሮች፣ ካዝናዎች፣ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ዩፒኤሶች ፣ የብር መቁጠሪያ ማሽኖች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች (የመሽ ወንፊት፣ የፋቢሪክ እና የቆዳ)፣ ጠረጴዛዎች፣ የብረት ፋይል ካቢኔቶች፣ ካዉንተር እና ኬጂ ከነ ጥበቃ ቤቶች እና ከሌሎች ቁርጥራጭ ብረቶች ጋር፣ አሉሚኒየም ፓርትሽኖች፣ የቅርንጫፍ ማስታወቂያ ታፔላዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነ በርሜሎቹ ጋር፣ አሮጌ ጋዜጣዎች፣ ባዶ የቶነር እቃዎች፣ የሽንት ቤት መቀመጫዎች እና የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች፣ የወለል የፕላስቲክ ታይልስ፣ ኮሪደሮች እና በረንዳ ላይ የሚቀመጡ የአበባ ማሳደጊያ ሳህኖች እና የመሳሰሉትን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል: – የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ። የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ሱሉልታ አካባቢ ሁለት ቦታ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች ሹፉኔ ቻይና ጋራጅ 100 ሜትር ገባ ብሎ አነን ሰላሌ የወተት ማቀነባበሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እና ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገዱ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ግንቦት 3፣ 5 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ። እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቄራ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ። ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ። ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
Closing Date
Check Details
ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’ ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ ጀነሬተሮች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁ. ብ/ባ/ፕ/ማ/ሎ-10/18 ብርሃን ባንክ አ.ማ. ታዳሽ የሃይል ምንጭ አማራጮችን የመጠቀም ስትራቴጂ ይዞ እየተገበረ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ ባለ 20 KVA ያገለገሉ ‘PERKINS’ ‘AKSA’ ‘CGM’ እና ‘LISTER’ ጀነሬተሮችን ለማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ጀነሬተሮች፤ ዝርዝራቸዉ፣ ብዛታቸዉ፣ የጨረታ መነሻ ዋጋቸዉ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሰነድ በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ ለጨረታ የቀረቡት ያገለገሉ ጀነሬተሮች የሚገኙት ገላን ከተማ ቱሉ ጉራቻ ቀበሌ ኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘዉ የባንኩ መጋዘን ሲሆን፣ ከታች በ9ነኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሱት ስልክ ቀጠሮች በቅድሚያ ደዉለዉ ቀጠሮ በማስያዝ ማየት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ግቢ 2ተኛ ፎቅ ከፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር በተገለፀዉ መሰረት ለሚጫረቱበት ጀነሬተር የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 10% ለእያንዳንዱ ጀነሬተር በተናጠል በብርሃን ባንክ ስም የተዘጋጀ C.P.O. ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ፤ ጀኔሬተሮች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ P.O ጋር፣ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝበት የቀድሞዉ ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ከነበረበት ቦታ ፊት ለፊት በሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት እና ሎጂስቲክስ አስተዳደር ቢሮ ለጨረታዉ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡ ጨረታዉ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን ባስገቡበት፣ በ5ተኛ ተራ ቁጥር በተጠቀሰዉ አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ባይገኙ በሌሉበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን ጀነሬተር/ጀነሬተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለዉ በመክፈል አሸናፊነታቸዉ በተገለፀላቸዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል፡፡ ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፣ 0918890721 / 0998411523 / 0114437439 / 0116631729 ይደዉሉ፡፡
Closing Date
Check Details
ስኬት ባንካ አ.ማ (የቀድሞ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ) ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና እንደተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ መስታወቂያ ስኬት ባንካ አ.ማ (የቀድሞ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ) ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸዉን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና እንደተሻሻለዉ አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ/ቁ የተበዳሪው ስም የዋሱ ስም የቤቱ ዓይነት ብድሩ የወጣበት ቅርጫፍ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት መነሻ ዋጋ ሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ ምርመራ ክ/ከተማ ወረዳ የቤቱ ካርታ ቁጥር የቦታ ስፋት በካ.ሜ ቀን ሰዓት 1 ፋሲካ መላኩ በራሳቸዉ መኖሪያ ኮንዶሚኒዬም ቤት ቃሊቲ ዱከም መልካ MDMW/356/05 25.33 1,160,747.25 26/08/2018 ዓ.ም 5፡00 ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ኤን.መብሬ.ኢንተ.ቢ.ግ.ሃ.የተ.የግ.ማ ሽታዬ ጋሻዉ ለንግድ ጎፋ አ/አ/ን/ስ/ላፍቶ 08 NL130141454109013347 109 3,728,791.79 28/08/2018ዓ.ም 4፡40 በድጋሚ 3 አብርሀም ፍቃዱ በራሳቸዉ መኖሪያ ቤት መርካቶ ፉሪ 01 Wt/24/2001 224 3,886,785.97 29/08/2018 5፡00 ለመጀመሪያ ጊዜ 4 ሰአዳ ነጋሽ በራሳቸዉ መኖሪያ ቤት ሰንዳፋ ሰንዳፋ በኬ 01 OR035011009012 205.10 2,104,205 30/08/2018ዓ.ም 5፡00 በድጋሚ 5 ፈለቀች ግርማ እሸት ከበደ መኖሪያ ቤት ኮ/ሴንተር ለገጣፎ/ ለገዳዲ ለገጣፎ/ ለገዳዲ OR00004092316005 143.66 5,294,534.72 04/09/2018ዓ.ም 4፡30 ለመጀመሪያ ጊዜ 6 ፈለቀች ግርማ ጊዜወርቅ ግርማ መኖሪያ ቤት ኮ/ሴንተር ለገጣፎ/ ለገዳዲ ለገጣፎ/ ለገዳዲ OR00004109818009 272.55 5,646,980.57 04/09/2018ዓ.ም 5፡30 ለመጀመሪያ ጊዜ ማሳሰቢያ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የቤቱን ሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መጫረት ይችላል ፡፡ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታዉን ማሸነፉቸዉን በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈሉ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም፡፡ የመኖሪያ ቤቶች ጨረታ መኖሪያ ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ይከናወናል፤የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታዉ መክፈቻ ስላሳ ደቂቃ ቀደም ብሎ ይጀመራል፡፡ ንብረቱ በገዢዉ ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተዉ መንግስት አካል ደብዳቤ ይፅፋል ፡፡ ቤቱን ለማየት ሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታዉ ከሚከናወንበት 5 (አምስት) ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት ህግ ክፍል በመመዝገብ ባንኩ በሚያመቻቸዉ ፕሮግራም ቤቶችን መጎብኝት ይቻላል ፤ በተጨማሪም ብድሩ በተሰጠበት ቅርጫፍ ፅ/ቤት በስራ ቀናት በመሄድ ቅርንጫፉ በሚሰጠዉ ፕሮግራም መሰረት መጎብኝት ይቻላል፡፡ ስም ማዘዋወሪያ፤የሊዝ ክፍያ እና ሌሌች ዉዝፍ ክፍያዎች እንዲሁም ገዥ እንዲከፈላቸዉ በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ገዥዉ/አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰዉ ቤት ላይ ካፒታል ጌን ታክስ አሸናፊዉ የሚከፈል ይሆናል፡፡ በጨረታዉ የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ጨረታውን ካካሄደዉ የባንኩ የሕግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይሆናል፡፡ በጨረታዉ ቀን የንብረቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ በመገኝት ጨረታዉን መከታተል ይችላሉ ባይገኙም ጨረታዉ ይካሄዳል፡፡ ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 8342 ወይም 011-1-279028 በመደወል ወይም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕግ አገልግሎት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
Closing Date
Check Details
The Development Bank of Ethiopia intends to sell the following properties that it has acquired from a defaulter pursuant to the power vested in it by proclamation No. 97/98, 216/2000 and 1147/2019.
Bid Announcement The Development Bank of Ethiopia intends to sell the following properties that it has acquired from a defaulter pursuant to the power vested in it by proclamation No. 97/98, 216/2000 and 1147/2019. S. N Name of former Borrower’s/ Guarantor’s Name Type (categorty) of Properties Plate No. Bid Floor Price (Birr) Property location Bid Type Date and Time of Bid 1 M2K Engineering PLC Machineries and equipment Birr 34,781,495.00 (Thrity Four Million Seven Hundred Eighty One Thousand Four Hundred Ninty Five Birr) Gelan town in the – M2K Engineering Factory Premises Negotiation May 11, 2026 From 10:00 – 12:00 AM 2 Office Furniture Birr 650,051.00 (Six Hundred Fifty Thousand Fifty One Birr) Gelan town in the – M2K Engineering Factory Premises Negociation May 12,2026 from 10:00-12:00 AM 3 Forklift Birr 210,396 (Two Hundred Ten Thousand Three Hundred Ninty Six Birr) 4 Generator Birr 697,151.00 (Six Hundred Ninty Seven Thousand One Hundred Fifty One Birr) 5 Mini bus 3-77195AA Birr 763,853.00 (Seven Hundred Sixty Three Thousand Eight Hundred Fifty Three Birr) Lega Tafo Legedadi town–(in the former MNS Textile Factory Premises 6 Mini bus 3-65018AA Birr 2,202,545.00 (Two Million Two Hundred Two Thousand Five Hundred Fourty Five Birr) 7 Cargo truck 3-77197AA Birr 410,562.00 (Four Hundred Ten Thousand Five Hundred Sixty Two Birr) Gelan town – in the M2K Engineering Factory premises 8 Cargo truck 3-77150AA Birr 342,940.00 (Three Hundred Fourty Two Thousand Nine Hundred Fourty Birr) 9 Cargo truck 3-77196AA Birr 345,355.00 (Three Hundred Fourty Five Thousand Three Hundred Fifty Five Birr) Instruction to bidders:- Interested bidders can obtain a complete bid document of the property, during office hours of the Bank upon payment of non-refundable fee of Birr 100.00 (Birr One Hundred) in cash, and fill out the bid document with their name, the offer price and other information as required by the format. The complete Wax-sealed bid document shall be received until May 11, 2026 9:50 A.M for machineries (Item-1) and May 12,2026 50 A.M for the others(Items #2-9), through bid placed at the Bank’s Head Office, second tower, ground floor starting from the third day of publication of this bid announcement. The bids shall open on May 11 and 12,2026 at 10:00 A.M Bidders shall submit 10% ( ten percent) of the floor price of the properties only in CPO as a bid security. A winner shall deposit the remaining winning price in full within 15 (Fifteen) calendar days from the date of award. Failure to deposit the amount within the specified time frame shall be a cause for loss of a bid security and cancellation of the award (bid). The bid shall take place at the Head Office of the Development Bank of Ethiopia, Tower Two, 5th Floor, on the date and time specified in the table above. Only the bidders or their authorized legal representatives shall be allowed to attend the bid process The winner is required to pay 15% VAT (Fifteen Percent Value Added Tax), and all other legal and administrative fees and charges in accordance with applicable laws. Some components of the properties have been procured under duty free scheme. Thus, the winner should either have matching custom duty exemption privilege or else shall be bound to pay the outstanding duties & taxes. The Bank intends to sell the properties on a cash basis only. The bank will write a letter to the concerned government body to facilitate transfer of the title of the properties to the buyer. It shall be the buyer’s responsibility to follow-through the process and get it finalised. The winner shall cover all costs of dismantling, loading unloading and transporting the properties to own distination. The properties are availed for sale separately as indicated under their respective serial numbers. bidders can obtain more information from the Development Bank of Ethiopia, Ongoing Concern Projects and Acquired Assets Management Directorate, 2nd Tower 3rd Floor or through telephone 011-524-53-73/011-524-42-69. Bidders can also visit the properties by making an appointment with the bank in advance.. The Bank reserves the right to cancel the bid partially or fully. THE DEVELOPMENT BANK OF ETHIOPIA
Closing Date
Check Details
ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ቤት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የመጀመሪያ የሐራጅ ማስታወቂያ ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ቤት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የአስያዡ ስም የንብረቱ አድራሻ የቦታው ስፋት በሜትር ካሬ የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ሐራጅ የሚከናወንበት ከተማ ክ/ከተማ እና ወረዳ የቤት.ቁ ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታው ሰዓት 1 ሽሬሻንሃይ ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አቶ አወል አብዱራሂም ኢብራሂም እና ወ/ሮ ባድራት አብደላ ኢብራሂም አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08 አዲስ 175 ካ.ሜ AA000060806472 ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል (G+1) ቤት ብር 14,433,563.52 (አስራ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከ52ሣ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30-5.00 ጠዋት 5.00-5.50 የሐራጅ ደንቦች፡- ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊው/ዋ የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው፡፡ አሸናፊው/ዋ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው፡፡ ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ፡፡ ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው፡፡ ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የንብረት ግብር፣ የቤት ማህበር መዋጮ፣ ውዝፍ ሊዝ ክፍያ፣ የአከራይ ተከራይ ግብር፣ ሌሎች ያልተከፈሉ ክፍያዎች ወዘተ (ካሉ) እነዚህን ክፍያዎች በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል፡፡ የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም፡፡ ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል፡፡ የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነ-ሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል፡፡ ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተ.ቁ 2 ላይ ያለውን ግዴታ እና የተቀሩት ግዴታዎችን ቀሪ አያደርግላቸውም፡፡ ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዥው ይከፍላል፡፡ የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሰንጋ ተራ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡ ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ቤት መጎብኘት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ዘመን ባንክ አ.ማ Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia
Closing Date
Check Details
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተ.ቁ የቀድሞ ተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም የንብረቶቹ ዓይነት ዝርዝር ታርጋ ቁጥር የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ የጨረታ ሁኔታ ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት 1 ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ማሽነሪዎች እና እኩፕመንት ብር 34,781,495.00 (ሰላሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አራት መቶ ዘጠና አምስት ብር) ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድርድር ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ምከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት 2 የቢሮ ዕቃዎች ብር 650,051.00 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ሃምሳ አንድ ብር) ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድርድር ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት 3 ፎርክሊፍት ብር 210,396 (ሁለት መቶ አስር ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር) 4 ጀነሬተር ብር 697,151 (ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ብር) 5 ቶዮታ ሚንባስ 3-77195 አአ ብር 763,853.00 (ሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ሦስት ብር) ለገጣፎ ለገዳዲ በቀድሞ ኤም ኤን ኤስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ 6 ቶዮታ ሚንባስ 3-65018 አአ ብር 2,202,545.00 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር) 7 ካርጎ ትራክ 3-01-77197 አአ ብር 410,562.00 (አራት መቶ አስር ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር) 8 ካርጎ ትራክ 3-77150 አአ ብር 342,940.00 (ሦስትመቶ አርባ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ብር) ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ 9 ካርጎ ትራክ 3-77196 አአ ብር 345,355.00 (ሦስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ሃምሳ አምስት ብር) ማሳሰቢያ፤ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ለማሽነሪዎች (ተ.ቁ 1) እና ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሎች ንብረቶች (ከተ.ቁ 2-9) ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ግንቦት 03 እና 04 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፤ ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ
Closing Date
Check Details
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ኤጋ ቆርቆሮዎችን፣ ፈርኒቸሮች፣ በሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ ጨርቆች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ የጨረታ ማስታወቂያ CN/DE/01/18 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ኤጋ ቆርቆሮዎችን፣ ፈርኒቸሮች፣ በሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ ጨርቆች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 300.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ ቀጠሮ በማስያዝ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት፣ ቃሊቲ በሚገኘው ጃቲ የዕቃ ግምጃ እንዲሁም አማልጋ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ከጨረታ ዋጋቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋርንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ስልክ ቁጥር 011-555 19 11 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Closing Date
Check Details
ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 ለባንኮችና ለማይክሮ ፋይናንስ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ Harbu Micro Finance Institution S.Co. የጨረታ ማስታወቂያ ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 ለባንኮችና ለማይክሮ ፋይናንስ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪዉ ስም የመያዣ ሰጭዉ ስም መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር የንብረቱ አገልግሎት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤ ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ 1 አየለ ቃሚሶ እና ኩሜ ቦሌ ባዩሽ በቀለ ባሌ ሐዋሳ ከተማ ታቦር ክ/ከተማ ፣ ጥልቴ ቀበሌ፣ የቤ.ቁ አዲስ 99 ካሬ መኖሪያ ቤት 3876 1,043,435.50/100(አንድ ሚሊዩን አርባ ሶስት ሺ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከ50/100) ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡00 ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት 2 ገረመው ነጋ ገረመው ነጋ ሐዋሳ ከተማ ቱራ ክ/ከተማ ፣ ዳቶ ቀበሌ፣ የቤ.ቁ አዲስ 200 ካሬ መኖሪያ ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር B143/4607 ፤ የቦታ መለያ B143/4607 ፤ 530,765.70/ አምስት መቶ ሰላሳ ሺ ሰባት መቶ ስልሳ አምስት ብር ከ70/100/ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡00-9፡00 ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት 3 ንጉሴ አገኘውና መሰረት ጴጥሮስ ዘውዴ ሳርሚሶ ሐዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፣ ዳካ ቀበሌ፣ የቤ.ቁ አዲስ 150 ካሬ መኖሪያ ቤት B6047/1228 4,000,000/አራት ሚሊዬን ብር/ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-5፡00 ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት ንብረቱ አይነት / መኖሪያ ቤት ማሳሰቢያ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከሚያዚያ 26 ቀን 2018 ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት አሊያም ደግሞ በተቋሙ ሀዋሳ ቅርንጫፍ መቀርቦ መውሰድ ይችላል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊወኪሉ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ሀያ አምስት በመቶ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በተቋሙ ስም በማሰራትና በማስያዝ አሊያም በጥሬ ገንዘብ በአካል ቀርቦ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ከፍተኛ ዋጋ የሠጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከተቋሙ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅኁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡ የጨረታው አሽናፊ /ገዥ/ አሸናፊነታቸው ከተቋሙ በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ ንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተቋሙ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ በተጠቀሱት ቀናት ቀሪውን ክፍያ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን ባይረከብ ጨረታው ዉጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ/ሲፒኦ/ ለተቋሙ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ/ ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች የሊዝ ክፍያን ጨምሮ ፤ ግብር ፣ በዋጋው ላይ የሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም፣ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ እና ሌሎች ወጪዎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዢው ይከፍላል:: ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ( የቀበሌ፤ የመንጃ ፈቃድ፤ እንዲሁም ብሄራዊ
Closing Date
Check Details
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚያካሂደው የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር አማራ ባንክ/35/2018 ሚያዚያ 21 ቀን በወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ ገጽ 17 ከተራ ቁጥር 5 እስከ 7 ያሉት የሀራጅ ማካሄጃ ቀን ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተብሎ የተጻፈው በስህተት ስለሆነ ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ግንቦት 21
የሐራጅ ማስታወቂያ ማስተካከያ አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚያካሂደው የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር አማራ ባንክ/35/2018 ሚያዚያ 21 ቀን በወጣው የሪፖርተር ጋዜጣ ገጽ 17 ከተራ ቁጥር 5 እስከ 7 ያሉት የሀራጅ ማካሄጃ ቀን ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተብሎ የተጻፈው በስህተት ስለሆነ ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ተብሎ የተስተካከለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ ጨረታው የሚከናወንበት ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ ቀበሌ ቀን ሰዓት ቦታ 5 ሀይማኖት ፈቃዴ ቢሻው ሀይማኖት ፈቃዴ ቢሻው ባህርዳር – ባህርዳር 11 200 ካሬ ሜትር 30/07/05 መኖሪያ 8,095,805.05 ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4-5 ሰዓት አማራ ባንክ ባህርዳር ዲሰትሪክት ጽ/ቤት (ባህርዳር ) 6 ዮሴፍ ነጋ ጌቱ ዮሴፍ ነጋ ጌቱ ባህርዳር ቡሬ ቡሬ – – 6300 ካሬ ሜትር BIAIP/006/2012 ፋብሪካ 20,003,475.78 ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ከ8- 9 ሰዓት አማራ ባንክ ባህርዳር ዲሰትሪክት ጽ/ቤት (ባህርዳር ) 7 አቮል የምግብ እና መጠጥ አቅራቢ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በላይነሽ ብርሃኑ ገ/ህወት በላይ ዘለቀ አፄ ቴዎድሮስ ባህርዳር – – 300 ካሬ ሜትር አፄቴ/9726/2015 መኖሪያ 22,312,051.97 ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ከ9- 10 ሰዓት አማራ ባንክ ባህርዳር ዲሰትሪክት ጽ/ቤት (ባህርዳር )
Closing Date
Check Details
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የአይቲ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA የጨረታ ማስታወቂያ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 010/2025/26 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የአይቲ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 11 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የተሽከርካሪና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የሚገኘው ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል፡፡ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡ ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል፡፡ የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች፣ የአይቲና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ለመጫረት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የማስወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Closing Date
Check Details