Tender Notice Board
Discover the latest public procurement and private sector tenders from across Ethiopia. Register to unlock full details.
Search Tenders
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የአይቲ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA የጨረታ ማስታወቂያ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 010/2025/26 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ተሽከርካሪ የመካኒካል መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ የኤሌክትሪካል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች፣ የሞተር ሳይክል ከመነዳሪዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የአይቲ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 11 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሚያዝያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የተሽከርካሪና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የሚገኘው ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል፡፡ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡ ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል፡፡ የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች፣ የአይቲና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ለመጫረት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የማስወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Closing Date
Check Details
ጸደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ታደሰ አላምረው የሰጠው ብድር ባለመመለሱ ባንኩ በዋስትና /በመያዣ/ የያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በድሮው ቀበሌ 07 በአሁኑ ቀበሌ 12 በወ/ሮ ጥሩድል ታደሰ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 200 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡
የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ ጸደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ታደሰ አላምረው የሰጠው ብድር ባለመመለሱ ባንኩ በዋስትና /በመያዣ/ የያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በድሮው ቀበሌ 07 በአሁኑ ቀበሌ 12 በወ/ሮ ጥሩድል ታደሰ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 200 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል ፡፡ ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ፡፡ የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 2,785,000 / ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ ብር / ነው ፡፡ በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት ፡፡ የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል ፡፡ የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል ፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው 1/4ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል ፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል ፡፡ የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡ ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ ፡፡ ጨረታው የሚካሄደው ደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 12 ለጨረታ በወጣው ንብረት ውስጥ ነው ፡፡ ጨረታው የሚካሄደው ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0921667115 /0912436868 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
Closing Date
Check Details
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንናበሠንጠረዡ የተመለከቱትንንብረቶችበአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) እና 1147/2011 መሠረት ባሉበትሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንናበሠንጠረዡ የተመለከቱትንንብረቶችበአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) እና 1147/2011 መሠረት ባሉበትሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ። የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚፈለግትን ክፍያ ከፍሎ ንብረቱን ካልተረከበ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ይመለስላቸዋል። ተበዳሪ/መያዣ ሰጪ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል። የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል። በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል። ጨረታው የሚካሄደው አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅየፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011515 0711 ወይም 011 515 1153በመደወል መጠየቅ ይቻላል። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ማሳሰቢያ፡- መጋዘኖቹ እና ማሽነሪዎቹ ተነጣጥለው አይሸጡም። ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የመያዣ ሰጪው ስም የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት የቦታው አጠቃላይ ስፋት በካ.ሜ የካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታ ሰዓት የጨረታው ሁኔታ 1. ቡሬ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማበር ተበዳሪው ለኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ አገልግሎቶች የሚውሉ 3 የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖች 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ካ.ሜ ገ/መ/አስ/መ14/2013 አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ የመጋዘኖቹ በድምሩ ብር 61,854,744.00 ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም 4:30-5:30 5፡30 -6፡00 በድጋሚ ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን —– የደረሰኝ ቁጥር 063፣057፣076፣081 እና 053 የማሽኑ ብር 12,000,000.00 ለመጀመሪያ ጊዜ 2. ምሳሌ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪው ለኢንዱስትሪ አገልግሎቶች የሚውሉ 5 የተለያየ ስፋት ያላቸው መጋዘኖች 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ካ.ሜ ገ/መ/አስ/መ07/2013 አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ የመጋዘኖቹ በድምሩ ብር 63,735,635.18 ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም 8:30-9:30 9፡30 -10፡00 ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ማሽን —– የደረሰኝ
Closing Date
Check Details
አዲስ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አዲስ ባንክ አ.ማ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር ማካካሻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ጨረታው በሚከናወንበት ቦታ በመገኘት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተ.ቁ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የቦታ ስፋት የንብረቱ ዓይነት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት ከተማ ክ/ከተማ 1 አዳማ ደምበላ ኢሬቻ ወረዳ 1000 ካሬ.ሜ G+4 ቅይጥ አገልግሎት 72,361,436.71 ሚያዚያ 15 ቀን 2018ዓ.ም ከሰዓት 8፡00- 9፡00 ሰዓት ማሳሰቢያ ፡- ቤቱን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ሚያዝያ 8፤9 እና 10 ቀን 2018ዓ.ም አዳማ ዲስትሪክት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በመገኘት ንብረቱን ማየት ይቻላል፡፡ ስልክ ቁጥር 0222 111562/0115570319፡፡ የጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም 25 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጨረታው ዕለት ይዞ በመምጣት መወዳደር ይቻላል፡፡ አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ተካታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል ፡፡ ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የክፍያ ሰነድ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ጨረታው ሚያዝያ 15 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ንብረቱ ባለበት ቦታ ይከናወናል፡፡ ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዘዋወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለውን አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡ ባንኩ ላሸነፉ ተጫራቾች ብድር ያመቻቻል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ አዲስ ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115 570319 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡ ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ አዲስ ባንክ አ.ማ
Closing Date
Check Details
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም የተሸከርካሪው አይነት የሚገኝበት አድራሻ የሰሌዳ ቁጥርና ሞተር ቁጥር የጨረታ መነሻ ዋጋ የጨረታዉ ቀንና ሰዓት ጨረታው የወጣው የመኪና ዓይነት የሚገኝበት ቦታ የሰሌዳ ቁጥር የተሰራበት ዘመን የሻንሲ ቁጥር የሞተር ቁጥር 1 አቶ ይድነቃቸዉ ተሰማ ወልደማርያም ተበዳሪው ህንድ-ሱዙኪ ዲዛይር አዲስ አበባ፣ሜክሲኮ(ሰንጋ ተራ) በሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ፤ አአ-03-B79598 2022 MBHCZF63S00335952 K12MP4350817 3,020,000.00 ሚያዚያ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 3:30-4:30 ሰዓት በድጋሚ 2 አልፋ ትሬድንግ ፓርትነርስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪዉ ሃዩንዳይ ቫን የጭነት ተሽከርካሪ አአ-3-A19890 2014 (ኢኤ.አ) KMFGA17CPFC284874 D4DCFJ591267 1,500,000.00 ሚያዚያ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከ 4:30-5:30 ሰዓት በድጋሚ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡ የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡ በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ታክስ ክፍያ ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 13 72 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ወይም ለተራ ቁ.1 በ 011-667-27-24 ኦሮሚያ ባንክ ቡርቃ ቅርንጫፍ፣ለተ.ቁ 2 በ 0115/504330 ቦሌ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡ ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ
Closing Date
Check Details
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥሮች 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፎቹ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥሮች 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ(ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡ ተራ ቁ. የተበዳሪ ስም የአስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ ቤቶቹ የሚገኙበት አድራሻና የቦታ ስፋት የንብረቱ የይዞታ ማረጋገጫ ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት 1 አቶ ብርሃኑ በላይ መኳንንት አቶ ብርሃኑ በላይ መኳንንት አብነት ሞጆ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 160 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 344/07 1,643,980.00 ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 2 አቶ ፈንታሁን በዜ ሽፈራው አቶ ፈንታሁን በዜ ሽፈራው ሞጣ ጎጃም፣ሞጣ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 5005/2013 1,697,059.00 ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 3 አቶ ይዘዘው ይላቅ ሞላ አቶ ይዘዘው ይላቅ ሞላ ገንደውሃ ጎንደር ከተማ፣ማራኪ ክፍለ ከተማ፣ቀበሌ 20፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ፣አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 14264/11 5,410,515.00 ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት 4 ወ/ሮ ውባገኝ መልኬ ታደሰ ወ/ሮ በልጣ እጂጉ ገንደውሃ ጎንደር፣ገንደውሃ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 192 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለሆቴል(ለንግድ) የሆነ ቤት በ 279/99 716,987.00 ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት 5 አቶ ነገስታት አንበርብር አወቀ አቶ ባበይ ቦጋለ እጂጉ ገንደውሃ ጎንደር፣ገንደውሃ ከተማ፣ቀበሌ 02፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለቅይጥ የሆነ ቤት በ=617/2011 770,376.00 ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት 6 ወ/ሮ ስምረት አብረሃ ገብረስላሴ ወይ/ ዓለምነሽ ዓሊ ገንደውሃ ጎንደር፣ገንደውሃ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለንግድ የሆነ ቤት አ=1833/2009 342,251.00 ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ወይ/ ሃብታም ደሳለኝ ዳኘው ገንደውሃ ጎንደር፣ገንደውሃ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 200 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት ሀ=340/2009 2,027,553.00 ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት 7 አቶ ፍቃዱ ለውጤ ዓለሙ አቶ ፍቃዱ ለውጤ ዓለሙ ደባርቅ ጎንደር፣ደባርቅ ከተማ፣ቀበሌ 03፣የቦታ ስፋት 250 ካ.ሜ፣ አገልግሎቱ ለመኖሪያ የሆነ ቤት 69/960/2006 1,580,845.00 ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ከ9፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት የሐራጅ ደንቦች፡- የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ.(Hibret Bank C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ(ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከቅርንጫፎቹ ወይም ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡ በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ንብረት ሐራጅ የሚካሄደው ንብ
Closing Date
Check Details
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ፀደይ ባንክ አ.ማ ለምቾት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና ዝርዝር ሁኔታቸው ከዚህ በታች የተገለጹትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪ ስም የንብረት አስያዥ ስም የንብረቱ መገኛ እና ካርታ ቁጥር መነሻ ግምት 1 ምቾት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር አቶ ታፈረ ወርቁ መራ በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ03 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16421/2013 መኖሪያ ቤት 2,487,661.37 2 ምቾት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር አቶ ታፈረ ወርቁ መራ በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 16422/2013 መኖሪያ ቤት 1,831,779.94 3 ምቾት ኃ/የተ/የግ/ ማህበር አቶ ታፈረ ወርቁ መራ በአብክመ በቡሬ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኝ ካርታ ቁጥር 9005//2008 መኖሪያ ቤት 2,119,342.42 በመሆኑም ማንኛቸውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ደንቦችና ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በጫራታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡ ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የድርጅቱን መመስረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ፤ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በ15 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ያሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ይመለስላቸዋል የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጭዎች ይሸፍናል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረው የሊዝ ክፍያ ገዡ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡ ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ፍኖተሰላም ከተማ ከሚገኘው የፀደይ ባንክ ፍኖተ ሰላም ዲስትሪክት ቢሮ ግራውንድ ይደረጋል ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918560275
Closing Date
Check Details
ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን መኖሪያ ቤት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት ይዞት የነበረ እና አሁን በእዳ የተረከበው በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር WB/PAF/06/26 ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን መኖሪያ ቤት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት ይዞት የነበረ እና አሁን በእዳ የተረከበው በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የንብረቱ ዓይነት ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ቤቱ/ሕንጻው ያረፈበት ቦታ በካ.ሜ ይዞታው ጠቅላላ ስፋት ከተማ ክ/ከተማ የቦታው ልዩ ስም የካርታ ቁጥር G+1 መኖሪያ ቤት ኦሮሚያ ሸገር ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ CCD (Country Club Developers) ግቢ ውስጥ OR042030709006 26,100,000.00 ምድር ቤት 259.95 ካ.ሜ 1ኛ ወለል 220.01 ካ.ሜ ሰርቪስ ቤት 54.10 ካ.ሜ 1,022.06 ካ.ሜ ማሳሰቢያ ተጫራቾች ከየትኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ብር 00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) በሒሳብ ቁጥር 0736452410101 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታው ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ መግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡ የመኖሪያ ቤቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሰረት መጎብኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መኖሪያ ቤቱን የሚገዙቡትን ዋጋ ¼ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻቸው እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. 8፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም። ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ዋጋ በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለባቸውም። የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት። አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፤ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም፡፡ ጨረታው ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ 9ኛ ወለል በባንኩ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከመኖሪያ ቤቱ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ የሚታሰብ ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ ወጪዎች፣ውዝፍ ክፍያዎች እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ወጭዎች የጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለበት። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን የማይረከብ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ማለትም እስከ 3ኛ ደረጃ ያልወጡ የጨረታ ግም
Closing Date
Check Details
የእናት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ የእናት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪ ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ ለጨረታው የቀረበው ንብረት የንብረቱዝርዝር የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ዓ.ም ሰዓት የሰሌዳ ቁጥር የስሪት ዘመን የሞተር ቁጥር የሻንሲ ቁጥር 1 አቶ ደሳለኝ ተፈራ ቢሰጥ አቶ ደሳለኝ ተፈራ ቢሰጥ ንግስት እሌኒ ሳሪስ ሱዙኪ ዲዛየር አአ- 3-B48458 2021 K12MP4310503 MBHZF6C1XNG191819 2,300,000.00 መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ከጧቱ 3:00-4:15 የሐራጅ ደንቦች 1 ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (¼ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ 2 የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝጊያ ሰዓት አስራ አምስት ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ የመጨረሻ አስራ አምስት ደቂቃዎች የተጫራቾች ምዝገባ አይካሄድም፡፡ 3 አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መከፈል አለበት፡፡ ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ 4 ሐራጁ ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ንብረቶቹ ባሉበት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሰንጋተራ ተብሎ በሚታወቀው በባንኩ የወደፊት ዋና መ/ቤት ህንፃ መገንቢያ ቦታ ይከናወናል፡፡ 5 በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ 6 በተሸከርካሪው ላይ ለመንግስት የሚከፈለው 15% የተ.እ.ታክስ እና ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ክፍያዎችን የስም ማዛወሪያ ጨምሮ ገዢው / አሸናፊው ይከፍላሉ፡፡ 7 ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 8 ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከአበዳሪው ቅርንጫፍ ጋር ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡ 9 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5-58-65-68 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
Closing Date
Check Details
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ የብድር መያዣ ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ የብድር መያዣ ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተ.ቁ የተበዳሪው ሙሉ ስም የመያዣ ስጪው ስም ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ የንብረቱ ዓይነትና አገልግሎት የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን የምዝገባ ሰዓት የጨረታ ሰዓት ጨረታው የወጣበት ጊዜ 1 አቶ በላይ ዳምጤ ተሾመ ተበዳሪው እስከ መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ብር 10,859,379.40 መኖሪያ ቤት 435 ካ.ሜ 46378/2014 ባህር ዳ ከተማ ጣና/ክ/ ከተማ ቀበሌ 16 20,667,474.00 ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00-5:30 5:30-6:00 ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ያሬንጃ የታሸጉ መጠጦች ጅምላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህር አቶ ተፈራ አላምራው ታዬ እስከ መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ብር 8,727,283.33 መኖሪያ ቤት 280 በቀድሞ 26085/2002 በአዲሱ የቁ/መ/ል/መለያ ኮድ AM00101041400 6 ባህር ዳር ከተማ አጼ/ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ቀበሌ 11 26,915,670.48 ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 5፡30-6፡00 ለመጀመሪያ ጊዜ 3 አቶ ይከበር ሞላ ሲሳይ ተበዳሪው እስከ መጋቢት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ብር 12,624,837.22 መኖሪያ ቤት 200 በቀድሞ 32157/07 በአዲሱ የቁ/መ/ል/መለያ ኮድ AM00105410201 1 ባህር ዳር ከተማ ዳ/ም ክ/ከተማ፣ ቀበሌ ሰላም 13,142,404.18 ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 5፡30-6፡00 ለመጀመሪያ ጊዜ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡: ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡ የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት/ንብረቶች መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችንም ገዢ ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡ ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት ይቻላል፡፡ በባንኩ ብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡ የጨረታው የሚከናወነው ንብረቶቹ በሚገኙበት ስፍራ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-96-60/ ወይም 09- 53-84-70-04 ባህር ዳር በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
Closing Date
Check Details
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ወጋገን ባንክ አ.ማ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር፡ ወጋገን 017/2018 ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል ተቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታው የሚከናወንበት ቀን ከተማ/ ክልል ክ/ከተማ/ ከተማ/ዞን ወረዳ /ቀበሌ 1 አቢሲንያ የቄራ አገልግሎት ኃ/የተ/ የግ/ማህበር አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ በቅሎቤት አዲስ አበባ የካ 13 500 ካ/ሜትር AA000051306364 መኖሪያ ቤት (G+2) 30,627,626.14 ሚያዝያ13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 – 6፡00 ሰዓት ማሳሰቢያ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡ ጨረታውን ላሸነፈ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ እንዲሁም ተጨማሪ የመያዣ ንብረት ለሚያቀርብ ተጫራች፤ ባንኩ በብድር መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡ የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡ በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በወጋገን ባንክ ዋና መስርያ ቤት ህንጻ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ይሆናል፡፡ ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡ ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ፡፡ ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡ ወጋገን ባንክ አ.ማ
Closing Date
Check Details
Hijra Bank S.C. hereby invites eligible and qualified national and international bidders to submit sealed bids for the supply and delivery of a 40 FT Containerized Data Center, Internet Banking Software, and Different IT Materials as per the specific
INVITATION TO NATIONAL & INTERNATIONAL COMPETITIVE BID Date: 22 April 2026Bid Name: Procurement of 40 FT Containerized Data Center, Internet Banking Software, and Different IT Materials. Hijra Bank S.C. hereby invites eligible and qualified national and international bidders to submit sealed bids for the supply and delivery of a 40 FT Containerized Data Center, Internet Banking Software, and Different IT Materials as per the specifications outlined in the Bidding Documents. S.N Item Description Lot Bid Closing Date and Time Bid Opening Date and Time Amount of Bid Security Specification & Quantity 1 40 FT Containerized Data Center Lot 1 May 7, 2026, at 11:00 AM (local time) May 8, 2026, at 3:30 PM (local time) 500,000.00 As specified in the bidding document 2 Internet Banking Software Lot 2 May 7, 2026, at 11:00 AM (local time) May 8, 2026, at 4:30 PM (local time) 300,000.00 As specified in the bidding document 3 Different IT Materials Lot 3 May 7, 2026, at 11:00 AM (local time) May 8, 2026, at 5:00 PM (local time) 300,000.00 As specified in the bidding document Hence, bidders are invited to participate in the supply of the above stated item. Interested and eligible bidders may obtain the bidding documents during office hours: Monday to Friday from 8:00 AM to 12:00 PM and 1:00 PM to 5:00 PM, and on Saturdays from 8:00 AM to 12:00 PM, commencing from April 22, 2026, to May 7, 2026. Documents can be collected from the Office of Facility and Supply Management, located at Olympia Square Road to Bambis, 1st Floor, New Building next to Hijra Bank. A complete set of bidding documents in English may be purchased upon payment of a non-refundable fee of Birr 500.00 (Birr Five Hundred only) for 40 FT Containerized Data Center, and Birr 300.00 (Birr Three Hundred only) each for the Internet Banking Software and Different IT Materials each. Payment should be made in cash at Hijra Bank S.C., Olympia Square, Nejeshi Branch. Bidders are required to submit copies of the following eligibility documents: renewed Trade License, VAT Registration Certificate, TIN Certificate, Manufacturer’s Authorization Letter, and FDRE Supplier Registration Certificate. The bid must be accompanied by a bid security in the amount specified in the table above. The bid bond shall be in the form of a CPO or an unconditional bank guarantee in the name of Hijra Bank, valid for 120 days. It must be submitted in a separate envelope attached to the technical proposal. Prices quoted shall remain valid for 90 days from the date of bid opening. Bidders shall submit complete bid documents enclosed in plain, sealed envelopes, clearly marked: “Supply and Delivery of a 40 FT Containerized Data Center, Internet Banking Software, and Various IT Materials.” The bids must be deposited in the designated Bid Box on or before May 7, 2026, at 11:00 AM (local time). Late submissions will not be accepted and will be returned unopened. The bid shall be submitted in one original, clearly marked “ORIGINAL,” and one copy, clearly marked “COPY.” Each envelope must be separately signed and sealed. In case of any discrepancy, the original shall prevail. Both envelopes shall then be enclosed in a single outer sealed envelope, clearly marked with the item description: “Supply and Delivery of a 40 FT Containerized Data Center.” Bids will be opened on the specified date and time indicated above at the Facility and Supply Management Office located at Olympia Square Road to Bambis, New Building, 1st Floor, next to Hijra Bank. Interested bidders are invited to attend the bid opening ceremony. Please note that the Bank will not facilitate foreign currency approval or Letters of Credit (LC). Bidders are expected to use their own sources, and all quotations must be in Ethiopian Birr. The Bank reserves the right to accept or reject any bid, in whole or in part, as it deems appropriate. For Further Information Interested bidders may obtain further information and the complete set of bidding documents from the address below: Hijra Bank S.C.Olympia Square, Road to Bambis1st Floor, New Building (Next to Hijra Bank)Office of Facility ManagementAddis Ababa, Ethiopia Tel: +251-11-558-4406P.O. Box: 1537 Code 1250
Closing Date
Check Details